ገድለ ታሪክ
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ — 600ኛ ዓመታቸውን በማስመልከት
የ14ኛው ክ/ዘመን ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ
የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ መናኝ ጻድቅ የህዝብ መምህርና የስነ ምህንድስና ባለሙያ የሆነው ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተወለዱት በ1357 ዓ.ም በቤተ አምራ በአሁኑ ወሎ ክፍለ ሀገር በከለላ ወረዳ ሸግላ (ሰግላ) በተሰኘች ቦታ ሲሆን አባታቸው ሕዝበ ጽዮን እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ።
፯ ነጥቦች
ስለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
ጥቂት ቢኖር እወዳለሁ
የአፄ ዳዊት ታሪክ
አፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስ የጻፉትን መጽሐፈ አርጋኖን በወርቅ ቀለም እስከ ማጻፍ የደረሱ የቅዱሱ አባት ወዳጅ ነበሩ።
በኋላ ግን ቢቱ የተባለ መናፍቅ በሐሰት ክስ አጣላቸውና አፄ ዳዊት የቢቱን ቃል አምነው አባ ጊዮርጊስን በደም እስኪሸፈኑ አስገርፈው ንጹሑን አባት በግፍ ወደ እስር ቤት አስወረወሩ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በእስር ቤት ሆነው ሳለ አፄ ዳዊት አርፈው ልጃቸው ቴዎድሮስ ቀዳማዊ እንደነገሠ ሲሰሙ እጅግ አዘኑ። ወዳጆቻቸውም «ያን ሁሉ ግፍ ያደረሰብዎት ንጉሥ ሞተ ሲባሉ ሊደሰቱ ሲገባ ስለ ምን ያዝናሉ?» ብለው ጠየቁ።
«እመቤታችንን የሚወድ ሰው ነውና ጥቂት ቢኖር እወዳለሁ።»
#አርጋኖን
በኃጢአት የቆሰለች ነፍስ ጸሎት
የሠራሁትን ኃጢአት ባስበው…
1 / 12
እመቤቴ የተመረጥሽ ድንግል ማርያም ሆይ በዕብራይስጥ ማርያም የተባልሽ አምላክ ካንቺ ጋራ በመሰደዱ በግብፅ መከራሽ እማልድሻለሁ።
ስለ እመቤታችን
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ፦
የደናግል መመኪያቸው የቅድስናቸው አክሊል ሆይ እኔን ከኃጥአን ሁሉ ይልቅ የረከስኩትን፤ አንቺን ከመውደድ በልጅሽ በወዳጅሽ በባሕርይ ሕይወቱ በመንፈስ ቅዱስ ከማመን በቀር ሌላ ትሩፋት የሌለኝን ይቅር በዪኝ ይቅር አሰኝኝ።
በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ የምሕረት ፈሳሽ ምንጭ የሚሆን ልጅሽን ኃጢአቴን እንዳያስብብኝ ለምኝው።
በኃጢአት ሁሉ እንደ እኔ ያለ በደለኛ የለም። እንደ ልጅሽም ቸር ሰው ወዳጅ ይቅር ባይ ከመዓት የራቀ ምሕረቱ የበዛ እውነተኛ የለም።
አንቺ ከተወለድሽ ጀምሮ ሰይጣን ፈጽሞ እረፍት አላገኘም። በአንቺ ታመመ በልጅሽም ተጨነቀ። በአንድ ልጅሽ መስቀል ሥቃይ አገኘው። ስለዚህ ከፍጡራን ወገኖች ሁሉ ይልቅ ሰይጣን አንቺን ይጠላል።
አባ ጊዮርጊስ ስለ ንስሐ
እኔም ብሠውረው ኃጢአቴ ሊከሰኝ ይጮኻል በደሌን ለማመን እኔ እንግዲህ ለምን ዝም እላለሁ? የሠራሁትም ክፉ ሥራዬ ያሳጣኛል እኔ እንዳልሠራ ለምን እሆናለሁ? የሚዘልፈኝ ምስክር አልሻም እኔ ለራሴ የራሴን ዘለፋ አነባለሁ እንጂ።
ለምን እሠውረዋለሁ? የማይሠወርልኝን ስለዚህ እንዲህ እላለሁ። ስለ ኃጢአቴ ራሴን ወደ ልዑል እግዚአብሔር አጠላለሁ።
ደግሞ እንዲህ አልሁ ኃጢአቴ ከራሴ ፀጉር በዝቷልና። እንደ ጽኑ ሸክም ከበደኝ…
ቅዱስ አባታችን በ1417 ዓ.ም በሐምሌ 7 ቀን ዐረፉ። በረከተ ጸሎታቸው ከሁላችን ጋር ይኑር — አሜን
