መጽሐፍት

«ብፁዕ ጊዮርጊስ የብሉይና የሐዲሳት ፍሬን ይሰበስባል»

የብርሃን ቤተ መጻሕፍት

የአባ ጊዮርጊስ መጻሕፍት

የእነዚህ መጻሕፍት ጸሐፊ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መሆናቸውን ያውቃሉ?

  1. ኆኅተ ብርሃን — የመጽሐፍ ሽፋን

    የብርሃን ደጅ

    ኆኅተ ብርሃን

    በእመቤታችን ሥዕል ፊት ተገልጦላቸው በሰባት ቀን የደረሱት፤ ከአርጋኖን ጋር የሚጸለይ የመጀመሪያ ድርሰታቸው። ሥዕሏ በደብረ ሐይቅ አሁንም ትገኛለች።

  2. መጽሐፈ አርጋኖን — የመጽሐፍ ሽፋን

    ምስጋና

    መጽሐፈ አርጋኖን

    በመንፈስ ቅዱስ ተገልጾላቸው ከብሉይ ኪዳን እስከ ዮሐንስ ራእይ ያሉትን ታሪኮች በመጥቀስ እመቤታችንን ከልጇ ጋር ያመሰገኑበት ድርሰት ነው።

  3. ውዳሴ መስቀል — የመጽሐፍ ሽፋን

    የመስቀሉ ክብር

    ውዳሴ መስቀል

    ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መስቀል አምጥተው ባዩ ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ልቡናቸውን አብርቶ ስለ መስቀሉ ክብርና ትርጉም የደረሱት ውዳሴ ነው።

  4. መጽሐፈ ብርሃን — የመጽሐፍ ሽፋን

    የብርሃን መንገድ

    መጽሐፈ ብርሃን

    የክርስቶስን አምላክነት፣ የእመቤታችንን ምስጋና፣ የቅዱሳንና የትጉሃን መላእክትን መንገድ ያሳያልና መጽሐፈ ብርሃን ተብሏል።

  5. መጽሐፈ ሰዓታት — የመጽሐፍ ሽፋን

    ዘመዓልት ወዘሌሊት

    መጽሐፈ ሰዓታት

    በየሰዓቱ የሚጸለይ ጸሎት — በቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥርዓት ላይ የተመሠረተ የቀንና ሌሊት አደራረስ። አጠቃላይ መዋቅሩ በአባ ጊዮርጊስ ተደረሰ።

  6. መዓዛ ቅዳሴ — የመጽሐፍ ሽፋን

    የቅዳሴ መጻሕፍት

    መዓዛ ቅዳሴ

    መናፍቃንን ተከራክረው ባሸነፉበት ጊዜ ጳጳስ ቅዳሴ እንዲደርሱ ፈቀዱ። መልክአ ቊርባንና ጸሎተ ፈትቶንም ደርሷል።

  7. መጽሐፈ ምሥጢር — የመጽሐፍ ሽፋን

    ለመናፍቃን መልስ

    መጽሐፈ ምሥጢር

    «ይኽን እኔ አልተናገርኩትም መንፈስ ቅዱስ አናገረኝ እንጂ» እስኪሉ በረቂቅ ምሥጢር የተሞላ ስለ ነበር መጽሐፈ ምሥጢር ተብሏል።

ሌሎች መጻሕፍት

  1. መጽሐፈ ፈውስ
  2. መጽሐፈ ባሕርይ
  3. መልክዐ ሥዕል
  4. መዝሙረ ድንግል
  5. ዕንዚራ ስብሐት
  6. ሕይወተ ማርያም
  7. ፍካሬ ሃይማኖት
  8. ውዳሴ ሐዋርያት
  9. ውዳሴ አምላክ
  10. ጠቢበ ጠቢባን
  11. ሊጦን
  12. መጥሔተ ድንግል መልክዓ ኤዶም
  13. በሰማይ ወምድር